Go to full page →

ከሙዚቃ የሚገኙ ጥቅሞች MYPAmh 189

የምስጋና ጣእመ ዜማ የሰማይ ከባቢ አየር ነው። ሰማይ ከምድር ጋር ሲነካካ ሙዚቃ እና ዝማሬ አለ “ምስጋናና የጣእመ ዜማ ድምፅ።” MYPAmh 189.1

አዲስ የተፈጠረችው ምድር ከእግዚአብሔር ፈገግታ ስር ሆና ያማረችና እንከን የለሽ ሆና በነበረችበት “የንጋት ኮኮቦች በአንድነት ዘመሩ፣ የእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ ደስታ ጮሁ።” ስለዚህ ሰማያዊ ልቦች ከሰማይ ጋር በመስማማት ለእግዚአብሔር መልካምነት በምስጋና ዝማሬ ምላሽ ሰጥተዋል። የሰብዓዊ ታሪክ አብዛኞቹ ክስተቶች ከመዝሙር ጋር የተገናኙ ናቸው…። MYPAmh 189.2