Go to full page →

የእግዚአብሔር ፀጋ መስመሮች MYPAmh 33

እግዚአብሔር ለዓለም ማስተላለፍ የሚችለውን የፀጋውን ብልፅግና፣ ያውም የክርስቶስን የማይመረመር ብልፅግና የማስተላለፊያ መስመር መሆን ለእያንዳንዱ ነፍስ መታደል ነው፡፡ ክርስቶስ የመንፈሱና የባህርዩ ወኪሎች ሆነው በዓለም ፊት የሚቀርቡትን ሰዎች የሚሻውን ያህል የሚሻው ሌላ ነገር የለም፡፡ ዓለም የክርስቶስ ፍቅር በሳብዓዊነት አማካይነት ሲገለጽ ለማየት የሚሻውን ያህል የሚሸው ሌላ ነገር የለም፡፡ ሰማይ በሞላ ለሰብዓዊ ልቦች ደስታና በረከት የሚሆን ቅዱስ ዘይት እየፈሰሰ የሚያልፍባቸውን ማስተላለፊያዎች ለማግኘት እየተጠባበቀ ነው፡፡—Christ’s Object Lessons, 419 MYPAmh 33.2