Go to full page →

የየግል ኃላፊነት MYPAmh 218

ልጆች ሆይ፣ ወላጆቻችሁ እንዲያስተምሩአችሁና እንዲያርሙአችሁ፣ እንዲሁም ባሕርያችሁን ለሰማይ በመመስረት ድርሻቸውን እንዲወጡ እግዚአብሔር እናንተን ለእነርሱ ጥንቃቄ አሳልፎ መስጠትን ገጣሚ (ተገቢ) እንደሆነ አይቷል፡፡ ሆኖም እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኝና የሚጸልዩ ወላጆች ስላሉአችሁ ያንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መልካም ክርስቲያናዊ ባሕርይን የማጎልበቱ ጉዳይ በእናንተ ላይ ያርፋል፡፡ ወላጆች ስለ ልጆቻቸው ያላቸው ስጋትና ስለ እነርሱ ያላቸውን ታማኝነት ባንክድም እነርሱ ብቻ ሊያድኑአቸው አይችሉም፡፡ ልጆች ራሳቸው ማድረግ ያለባቸው ሥራ አለ፡፡ እያንዳንዱ ልጅ መፈጸም የሚገባው የየግል ጉዳይ አለ፡፡ MYPAmh 218.4

እናንተ አማኝ ወላጆች በሃይማኖታዊ ልምምዳቸውም ቢሆን የልጆቻችሁን እርምጃዎች እንድትመሩ ከፊታችሁ ኃላፊነት የሚጠይቅ ሥራ አለ፡፡ እነርሱ እግዚአብሔርን በእውነት ሲወዱት እናንተ ላደረጋችሁላቸው ጥንቃቄና ፍላጎታቸውን በመግታትና ፈቃዳቸውን በማስገዛት ላሳያችሁት ታማኝነት ይባርኩአችኋል፣ ያከብሩአችኋልም፡፡ Testimonies for the church, vol.1, P. 391-403 MYPAmh 218.5