Go to full page →

በየቀኑ ወደ ፊት መጓዝ MYPAmh 36

በየቀኑ ወደፊት መጓዝ የወጣቶች ሥራ ነው፡፡ ጴጥሮስ እንዲህ አለ፡- «በእምነታችሁ ላይ ደግነትን ጨምሩ፣ በደግነት ላይ እውቀትን፣ በእውቀት ላይ መሻትን መግዛትን ፣መሻትን በመግዛት ላይ ትዕግስትን ፣ በትዕግስት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን፣ እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ ወንድማዊ ፍቅርን፣ በወንድማዊ ፍቅር ላይ በጎነትን ጨምሩ፡፡ እነዚህ ነገሮች በእናንተ ውስጥ ቢኖሩና ቢበዙ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ባዶዎችና ፍሬ ቢሶች አትሆኑም፡፡» MYPAmh 36.2

እነዚህ ተከታታይ ደረጃዎች በዓይነ ህሊና ፊት መሆንና እናንተ እንደ ጀመራችሁት ጅምር መቆጠር የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ዓይኖቻችንን በኢየሱስ ላይ በማድረግና በእግዚአብሔር ክብር ላይ በማተኮር ወደፊት መጓዝ ትችላላችሁ፡፡ ወደ ክርስቶስ ሙሉ ሰውነት ደረጃ በአንድ ቀን መድረስ አትችሉም፡፡ በመሆኑም በየቀኑ የሚያጋጥሙአችሁን ልታሸንፉአቸው የሚገባችሁን ችግሮች ስታዩ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ትሰምጣላችሁ፡፡ ሊገዳደራችሁ ያለ ሰይጣን ስላለ እያንዳንዱን ሊያገኛችሁ የሚችለውን መሳሪያ በመጠቀም አእምሮአችሁን ከክርስቶስ እንድታነሱ ለመሳብ ይፈልጋል፡፡ MYPAmh 36.3