Go to full page →

ከፍታዎቹን መውጣት MYPAmh 36

ፍፁም የሆነ የክርስቲያን ባህሪይን በመመስረት ረገድ ትክክል በሆነ ስራ መቀጠል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በወጣቶቻችን አእምሮ ባህርይን በመገንባት ስራ ትጋትና ጥረት አስፈለጊ መሆናቸውን ማስቀመጥ እፈልጋለሁ፡፡ ወጣቶች ከፍ ወዳለው ሰውነት ደረጃ እንዲደርሱ ከልጅነት እድሜያቸው ጀምሮ በባህርያቸው ውስጥ ክርስቲያናዊ መርሆዎችን መሸመን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ሁል ጊዜ በዓይኖቻቸው ፊት በዋጋ መገዛታቸውንና እግዚአብሔርን በራሱ በሆኑት በአካላቸውና በመንፈሳቸው ማክበር እንዳለባቸው ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ MYPAmh 36.1