Go to full page →

ሃይማኖት በአለባበስ ሲፈረድ MYPAmh 225

ውድ ወጣቶች፣ እንደ ወቅቱ ፋሽን ለመልበስና ለታይታ የሚደረጉ ሐብል፣ ወርቅና ብልጭልጮችን ለማድረግ በውስጣችሁ ያለው ፍላጎት ሃይማኖታችሁንም ሆነ እናምናለን የምትሉትን እውነት ለሌሎች አይገልጽም፡፡ ትክክለኛ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች ውጫዊ ማንነታቸውን ለማስዋብ የምታደርጉትን ጥረት ደካማ አእምሮና ኩሩ ልብ ያላችሁ ለመሆናችሁ እንደ ማረጋገጫ አድርገው ይወስዳሉ፡፡ ወጣት እህቶቻችን ቀላል፣ ያላሸበረቀና ማስመሰል የሌለበትን አለባበስ እንዲለብሱ ይመከራሉ፡፡ ብርሃናችሁ ለሌሎች እንዲበራ ለማድረግ በአለባበሳችሁና ራሳችሁን በማስዋብ ረገድ ቀለል ያለ መንገድን ከመከተል የተሻለ ሌላ መንገድ የለም፡፡ ከዘላለማዊ ነገሮች ጋር ሲነጻጸር ለምድራዊ ነገሮች ተገቢ የሆነ ግምት እንደምትሰጡ ለሁሉም ሰዎች ማሳየት ትችላላችሁ፡፡ Testimonies for the church ,vol..3, P. 376. MYPAmh 225.5