Go to full page →

እርካታ ያላገኙ ናፍቆቶች MYPAmh 239

ደስታን ይሰጣሉ ለተባሉ መደሰቻዎች ያለው የማያቋርጥ ናፍቆት የነፍስን ጥልቅ ምኞት የሚገልፅ ነው። ነገር ግን ከዚህ ዓለማዊ የደስታ ምንጭ የሚጠጡ ሰዎች አሁንም ነፍሳቸው ሳትረካ እንደተጠማች ያገኙአታል። እነርሱ ተታልለዋል! ፈንጠዝያንና ደስታን አምታትተዋል! ጊዜያዊው መነቃቃት ሲያበቃ ብዙዎች ወደ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ ይሰምጣሉ። ውኃ መቋጠር ለማይችሉ (ለተሸነቆሩ) የዓለም ደስታ ጉድጓዶች በማለት የሕይወት ውኃ ምንጭን መተው ምን አይነት እብደት ነው! እንዴት ያለ ሞኝነት ነው! Fundamentals of Christian Education, P. 422. MYPAmh 239.6