Go to full page →

እውነተኛ ገርነት ይፈለጋል MYPAmh 268

የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያውቁ ወንዶችና ሴቶች በእርሱ ሥራ ውስጥ የተሳካላቸው ሠራተኞች እንዲሆኑ የማስተማር ከፍተኛ አስፈላጊነት አለ። እነርሱ በደንብ የተሞረዱ፣ አስተዋዮች፣ ዓለማዊ የሆነ ውጫዊ ብልጭልጭ ወይንም የማስመሰል ፈገግታ የሌላቸው ግን የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይ የሆነ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሊኖረው የሚችል የባሕርይ ውበትና እውነተኛ ገርነት ያላቸው መሆን አለባቸው። እውነተኛ የሆነ ክብርና ክርስቲያናዊ የባሕርይ ንፅህና በሰንበት ጠባቂዎች መካከል መጥፋት እኛ እንደ ህዝብ ተቀባይነት እንድናጣ የሚያደርግና እናምናለን የምንለው እውነት የተጠላ እንዲሆን የሚያደርግ ነው። አእምሮንና ባሕርይን የማሰልጠን ሥራ እስከ ፍጽምና የሚዘልቅ ሥራ ነው። አሁን እውነቱን እንቀበላለን የሚሉ ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ሙሉ መንፈሳዊ የእድገት ደረጃ ለመድረስ የተሰጣቸውን መልካም •እድልና አጋጣሚዎች ካልተጠቀሙ በስተቀር ለእግዚአብሔር ሥራ ክብር ሊያመጡ የማይችሉና ኢየሱስን የማያከብሩ ይሆናሉ። Testimonies for the Church, vol. 4, pp. 358-359. MYPAmh 268.4