Go to full page →

በሳል ውሳኔ አስፈላጊ ነው። MYPAmh 280

የህብረተሰብ ደህንነትና የተማሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት ባሕርያቸው ሳያድግ፣ በሳል ውሳኔ ማድረግ ሳይችሉና የወላጆች ጥንቃቄና አመራር ሳይደረግላቸው የህይወት ጓደኛን ለመምረጥ ጥረት ማድረግ እንደሌላባቸው ይጠይቃል። MYPAmh 280.4

ወጣቶችን ከፈተና ለመጠበቅና ለጠቃሚ ሕይወት ለማዘጋጀት የሚሹ ሰዎች መልካም ሥራ እየሠሩ ናቸው። በማንኛውም ተቋም ወጣቶችን በደንብ የመቆጣጠርና የማረም ግንዛቤዎች መኖራቸውን ስናይ በጣም ደስ ይለናል። የእነዚህ ዓይነት መምህራንን ጥረቶች እግዚአብሔር በክንውን ያጎናፅፋቸው። Fundamentals of Christian Beliefs, P. 62-63. MYPAmh 280.5