Go to full page →

ለእናቱ ያለው እንክብካቤ ማነፃፀሪያ MYPAmh 284

እውነተኛ ፍቅር እንክብካቤ የሚያሻው ተክል ነው። ለወደፊት ሰላማዊና ደስተኛ ህብረት እንዲኖራትና ሐዘንና ሥቃይን ማምለጥ የምትፈልግ ሴት ፍቅርን ከመስጠቷ በፊት እነዚህን ጥያቄዎች ትጠይቅ። ፍቅረኛዬ እናት አለችውን? እሷ ያሳደረችበት አሻራ ምንድነው? ለሷ ያለውን ግዴታ ይረዳልን? የሷ ፍላጎትና ደስታ ይገደዋልን? እናቱን የማይወድና የማያከብር ከሆነ ለሚስቱስ አክብሮት፣ ፍቅር፣ ትህትናና ትኩረት ይሰጣልን? በስህተቶቼ ይታገሠኛል ወይስ ወቃሽ፣ የሚያጎላና አምባገነን ይሆናል? እውነተኛ ፍቅር ብዙ ስህተቶችን ያልፋል። ፍቅር በእነዚህ ስህተቶች ላይ አያተኩርባቸውም:: MYPAmh 284.3