Go to full page →

ስሜት አይታመንም MYPAmh 284

ወጣቶች ስሜታቸውን ያለ መጠን ያምኑታል። ራሳቸውን በቀላሉ መስጠት የለባቸውም፣ እንዲሁም በፍቅረኛቸው ውጫዊ አቀራረብ በቀላሉ መማረክ የለባቸውም። ከጋብቻ በፊት ያለው የፍቅረኞች ግንኙነት በዘመኑ የማታለልና የግብዝነት ስልት ነው። በዚህም ምክንያት ከጌታ ይልቅ የነፍሳት ጠላት ብዙ ያደርጋል። በዚህ ነጥብ ላይ ጥሩ ግንዛቤ ያስፈልጋል። MYPAmh 284.4

ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር ቢቀራረቡ፣ ቢታመኑባቸው፣ ደስታቸውንና ሃዘናቸውን ቢያካፍሉአቸው ኖሮ ከብዙ የወደፊት ራስ ምታት ራሳቸውን ያድኑ ነበር። ትክክለኛው እርምጃ የትኛው እንደሆነ ግራ ሲገባቸው ጉዳዩን እነርሱ እንዳገኙት በወላጆቻቸው ፊት አቅርበው ምክር ይጠይቁ። እግዚአብሔርን እንደሚፈሩ ወላጆች የተመቻቸና ከፊታቸው ያለውን አደጋ መጠቆም የሚችል ማን አለ? የእነርሱን ያህል የልጆቻቸውን አመል የሚያስተውል ማን አለ? MYPAmh 284.5

ክርስቲያን የሆኑ ልጆች ከማንኛውም ምድራዊ በረከት ይልቅ ለወላጆቻቸው ፍቅርና መስማማት የበለጠ ቦታ ይሰጣሉ። ወላጆች ለልጆቻቸው ያዝናሉ፣ ይፀልያሉም። እግዚአብሔር እንዲጠብቃቸውና እንዲመራቸው አብረው ይፀልያሉ:: ከሁሉም የበለጠ በድካማቸው ወደሚሰማቸውና ወደማያልፈው ጓደኛቸውና አማካሪያቸው ያመላክቱአቸዋል። ያለ ኃጢአት ከመሆኑ በቀር በሁሉም እንደኛ የተፈተነ ስለሆነ በፈተና ያሉትን እንዴት እንደሚረዳቸው ያውቃል። Review and Herald, Jan. 26,1886. MYPAmh 284.6