Go to full page →

ከማያምኑ ጋር መጠመድ MYPAmh 287

ዓለማዊ ህብረት መፍጠር አደገኛ ነገር ነው። ብዙ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ጋብቻ የሚፈጽሙበት ሰዓት የኃይማኖት ልምምዳቸውንና ጠቃሚነታቸውን ታሪክ እንደሚዘጋ ሰይጣን በደንብ ያውቃል። ለጊዜው ክርስቲያናዊ ህይወትን ለመኖር ጥረት ያደርጉ ይሆናል፣ ነገር ግን ጥረታቸው በሌላ በኩል ያለውን የማያቋርጥ ተፅእኖ የሚቃወም ነው። አንድ ጊዜ ስለ ደስታቸውና ተስፋዎች መናገርን እንደ መልካም አጋጣሚ ቆጥረወት ነበር፤ ነገር ግን ብዙም ሳይቆዩ ለሕይወት ዘመናቸው የተጣመሩት ግለሰብ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ፍላጎት የሌለው መሆኑን በመገንዘባቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ማውራት አይፈልጉም። በመሆኑም ሰይጣን በስውር የጥርጣሬ መረብን በዙሪያቸው ይጠላልፍና በከበረው እውነት ላይ ያለው እምነት ከልብ ውስጥ ይሞታል። MYPAmh 287.4

ወጣቶችን በኃጢአት ውስጥ ማቆየት የሰይጣን የተጠና ጥረት ነው። ይህን ማድረግ ሲችል ሰይጣን በሰውየው ጥፋት እርግጠኛ ይሆናል። የነፍሳት ጠላት ወጣቶችን በትክክለኛ አቅጣጫ የመምራትን ጥረት በጣም ይጠላል። የክርስቶስንና የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ሐሳብ የሚሰጠንን ነገር ሁሉ ይጠላል። በተለይም የእርሱ ጥረት የሚያተኩረው ከሰማይ ብርሃንን ሊቀበሉ በሚችሉበት ቦታ በተቀመጡት ላይ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ለመፍጠር በእነርሱ በኩል የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ፈተናውን ለመቋቋም ኃይል እንደሚሰጣቸው ስለሚያውቅ ነው። በብርሃን መልአክ ተመስሎ የማታለያ ወጥመዶቹን በመያዝ ወደ ወጣቶች ይመጣና ብዙ ጊዜ ደረጃ በደረጃ ከተግባራቸው ማዘናጋት ይሳካለታል። MYPAmh 287.5