Go to full page →

የችኮላ ጋብቻ MYPAmh 288

ሰይጣን ልምድ የሌላቸውን ወጣቶች ወደ ጋብቻ ህብረት በጥድፊያ እንዲገቡ ለማድረግ ሁልጊዜ በትጋት ይሠራል። ዛሬ እየተፈፀሙ ባሉ ጋብቻዎች ብዙ ባንኮራባቸው መልካም ነው። ነገር ግን የጋብቻ ቅዱስነት ሲስተዋል ለዚያ ጋብቻ ዛሬም ቢሆን ሰማይ ለትክክለኛነቱ ማረጋገጫ ይሰጣል። ውጤቱም የሁለቱ ተጋቢዎች ደስታ ሲሆን እግዚአብሔርም ይከብርበታል:: MYPAmh 288.1

እውነተኛ ሐይማኖት አእምሮን የከበረ ያደርጋል፣ ፍላጎትን ያስተካክላል፣ አመለካከትን ይቀድሳል፣ አማኙን የሰማይ ንፅህናና ተፅእኖ ተካፋይ ያደርገዋል። መላእክትን ወደ አጠገቡ በማምጣት ከዓለም ተፅእኖ የበለጠ እንዲለይ ያደርጋል። Testimonies for the Church, Vol. 2, P. 252 -253. MYPAmh 288.2