Go to full page →

የእውነተኛ ፍቅር ባሕርያት MYPAmh 290

ፍቅር ምንጩ ሰማይ የሆነ ተክል ነው። እውነተኛ ፍቅር ምክንያት የለሽ ወይም እውር አይደለም። ንፁህና ቅዱስ ነው። ነገር ግን የተፈጥሮዓዊ ልብ ስሜት ሌላ ነገር ነው። እውነተኛ ፍቅር እግዚአብሔርን በዕቅዶቹ ሁሉ የሚያስገባና ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር የሚስማማ ሲሆን ስሜት ደግሞ ደንዳና፣ ችኩል፣ ምክንያት የለሽ፣ ቁጥጥርን የሚቃወምና የራሱን ምርጫ ጣዖት የሚያደርግ ነው። MYPAmh 290.5

የእግዚአብሔር ፍቅር ባለው ሰው በፀባዩ ሁሉ የእግዚአብሔር ፀጋ ይታያል። ጨዋነት፣ ራስን ዝቅ ማድረግ፣ እውነተኝነት፣ ግብረ ገብነትና ሐይማኖት ወደ ጋብቻ የሚመራውን እያንዳንዱን እርምጃ ይከተለዋል። ስለዚህ በዚህ ዓይነት ፍቅር ቁጥጥር ስር ያሉ በፀሎት ስብሰባዎችና የሐይማኖት አገልግሎቶች ፍላጎት በማጣት በእያንዳንዳቸው ግንኙነት ይመሰጣሉ። MYPAmh 290.6