Go to full page →

መለኮታዊ አመራርን መሻት MYPAmh 291

ወንዶችና ሴቶች ጋብቻን ከማሰባቸው በፊት በቀን ሁሉት ጊዜ የመፀለይ ልምድ ካላቸው የዚህ አይነት እርምጃን ለመውሰድ ሲያስቡ በቀን አራት ጊዜ ይፀልዩ። ጋብቻ በሕይወትህ ላይ በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ዓለም ተፅዕኖ የሚያሳድር ነገር ነው። እውነተኛ ክርስቲያን እርምጃውን እግዚአብሔር ያረጋገጠለት መሆኑን ሳያረጋግጥ በዚህ አቅጣጫ ወደ ፊት አይገፋም። ለራሱ መምረጥ አይፈልግም! ነገር ግን እግዚአብሔር ሊመርጥለት እንደሚገባ ይሰማዋል። ክርስቶስ እራሱን ስላላስደስተ እኛም እራሳችንን ለማስደሰት መኖር የለብንም:: ማንም ሰው የማይወደውን ሰው ያግባ ማለቴ እንዳልሆነ እንድታስተውሉ እሻለሁ። የማትወዱትን ሰው ማግባት ኃጢአት ነው። ነገር ግን ከእውነት የራቀ ሀሳብና ስሜት ወደ ጥፋት እንዲመራችሁ መፍቀድ የለባችሁም። እግዚአብሔር ሙሉ ልብን፣ ከሁሉም የበለጠ ፍቅርን ይሻል። MYPAmh 291.1

አብዛኞቹ የዘመናችን ጋብቻዎችና እነዚህ ጋብቻዎች የሚፈፀሙበት መንገድ የዘመን መጨረሻ አንዱ ምልክት ያደርጋቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልበ ደንዳኖችና በፍላጎታቸው ግትር ስለሆኑ እግዚአብሔር ከጥያቄ ውጭ ሆኗል። ሐይማኖት በዚህ ክቡርና አስፈላጊ በሆነ ነገር ላይ ምንም ድርሻ እንደሌለው ተቆጥሮ ወደ ጎን ተትቷል። ነገር ግን እውነትን እናምናለን የሚሉ ሰዎች በእውነቱ ካልተቀደሱና በአስተሳሰብና በባሕርይ ከፍ ካላሉ በስተቀር በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ጉዳይ ላይ ብርሃንን በፍፁም አግኝቶ ከማያውቅ ኃጢአተኛ በምንም መንገድ በተሻለ ሁኔታ ውስጥ አይደሉም። Review and Herald, September 25,1888 MYPAmh 291.2