Go to full page →

የጋብቻ ሃላፊነቶች MYPAmh 292

ውርስም ሆነ ንብረት ሳይኖራቸው ብዙ ሰዎች ወደ ጋብቻ ገብተዋል። ንብረትን ለማፍራት የሚያስችል የአካል ብርታትም ሆነ የአእምሮ ኃይል የላቸውም። እነዚህ ሰዎች ለማግባት የሚቸኩሉና ከዚህ በፊት ተሰምቶአቸው የማያውቀውን ሃላፊነት በራሳቸው ላይ እያመጡ ያሉ ናቸው። የከበረና ከፍ ያለ ስሜት የላቸውም፣ ቅን የሆነ የባለቤትነትና የአባትነት ተግባር እውቀትም የላቸውም። የቤተሰብን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስከፍለው ዋጋ ምን እንደሆነም እውቀት የላቸውም:: የቤተሰብ ቁጥር መጨመርን በተመለከተ ከንግዳቸው መጨመር የበለጠ ትክክለኛነትን አያሳዩም…። MYPAmh 292.1

የጋብቻ ተቋም ለሰው በረከት እንዲሆን ሰማይ ያቀደው ነው። ነገር ግን በአጠቃላይ ሲታይ አሰቃቂ እርግማን እስኪሆን ድረስ በስህተት ጥቅም ላይ ውሏል። መልስ ማግኘት ያለበት ጥያቄ የእርስ በርስ መዋደድ ብቻ እንደሆነ በመቁጠር ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደ ጋብቻ ህብረት ገብተዋል። ነገር ግን የጋብቻ ሀላፊነት ከዚህ በላይ መሆኑን መገንዘብ አለባቸው። ልጆቻቸው የአካል ጤንነትና የአእምሮና የሞራል ፅናት እንደሚኖራቸው ማሰብ አለባቸው። ነገር ግን በቀላሉ ችላ ሊሉት በማይችሉት ከፍ ያለ ምክንያትና አመለካከት የተነሱት ጥቂቶች ናቸው። ህብረተሰቡ ከእነርሱ የሚጠብቅ ነገር እንዳለውና የቤተሰባቸው ተፅእኖ ሚዛን ወደ ላይ ወይም ወደ ታች እንደሚመዘን ከግምት ያስገቡት ጥቂቶች ናቸው። A Solemn Appeal, P. 63-64. (Edition: Signs Publishing Company Limited). MYPAmh 292.2