Go to full page →

ራስን የመቆጣጠር አስፈላጊነት MYPAmh 293

ባልና አባት የሆነ ሰው በተፈጥሮ ውስጥ ያለው እንስሳ ህሊናንና ግብረ ገብን እንዲቆጣጠር (እንዲገዛ) በመፍቀዱ ምክንያት ብዙ ቤተሰቦች እጅግ ደስታ በራቀው ሁኔታ ውስጥ ይኖራሉ። ከዚህ የተነሣ ብዙ ጊዜ የድካምና ተስፋ የመቁረጥ ስሜቶች የሚታዩ ቢሆንም ለዚህ አስተዋፅም ያደረገው የራሳቸው የተሳሳተ ድርጊት መሆኑን አይገነዘቡም። ለሰብአዊ ዘር ጥቅምና ለእግዚአብሔር ፍፁም አገልግሎትን ለመስጠት እንድንችል መንፈሳችንን ንፁህና አካላችንን ጤናማ አድርገን ለእግዚአብሔር የማቆየት ግዴታ አለብን። Testimonies for the Church, Vol. 2, P. 380 -381. MYPAmh 293.5