Go to full page →

እግዚአብሔር እንድንደርስ MYPAmh 49

ያስቀመጣልን ከፍ ያለ ደረጃ እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩ ከሚናገሩ ወጣቶች መካከል የብዙዎቹ ሁኔታ ይህንን አረፍተ ነገር የሚቃረን ይመስላል፡፡ በእውቀትም ሆነ በመንፈሳዊነት እድገት አያሳዩም፡፡ ያሉዋቸው ችሎታዎች በማደግ ፋንታ ቀጭጨዋል ፡፡ ነገር ግን የባለ መዝሙሩ ቃላቶች ለእውነተኛ ክርስቲያን እውነት ናቸው፡፡ ይህ በርግጥ ብርሃንና ማስተዋል የሚሰጥ ተራ የእግዚአብሔር ቃል ደብዳቤ ብቻ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለልብ የተከፈተና የተሰጠ ቃል ነው፡፡ ሰው በእውነት ሲለወጥ የእግዚአብሔር ልጅና የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይ ይሆናል፡፡ የሚታደሰው ልብ ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ችሎታም ይነቃቃና ብርታት ያገኛል፡፡ ከመለወጣቸው በፊት ተራና ዝቅ ያለ ችሎታ የነበራቸውና ከተለወጡ በኋላ ሙሉ በሙሉ አዲስ ሰው የሆኑ ሰዎችን ሁኔታ የሚገለፁ ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ ፡፡ ከፍተኛ የአእምሮ ችሎታ የነበራቸው ሰዎች ከእነዚህ ሰዎች ጋር መነጋገርን እንደ መልካም እድል አይተዋል፡፡ MYPAmh 49.2

የጽድቅ ፀሐይ ብሩህ የሆነ ጨረሩን በአእምሮአቸው ውስጥ በማሳረፍ እያንዳንዱን ኃይላቸውን ለብርቱ ተግባር ቀስቅሷል፡፤ ወጣቶች በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ቃሉን በልባቸው ቢቀበሉና በሕይወታቸው ቢታዘዙት ኖሮ እግዚአብሔር ለወጣቶች ታላቅ ነገር ያደርግ ነበር፡፡ የጥበብ፣ የበጎነት፣ የንጽህናና የእውነት ሁሉ ምንጭ የሆነው ወደ ራሱ ሊስባቸው ሁል ጊዜም እየፈለገ ነው፡፡ በከበሩ ሐሳቦች የተሞላ አእምሮ ራሱ ይከብራል፡፡ MYPAmh 49.3