Go to full page →

በፈተና እርዳታ MYPAmh 50

በእምነትና በፀሎት ሁሉም የወንጌልን መስፈርት ማሟላት ይችላሉ፡፡ ማንም ሰው ህግን እንዲጥስ አይገደድም፡፡ በመጀመሪያ የራሱ መስማማት መኖር አለበት፡፡ ፍትወት የአእምሮ የማገናዘብ ችሎታን ከማሸነፉ በፊት ወይም ኃጢአት በህሊና ላይ ድልን ከመቀዳጀቱ በፊት ነፍስ የኃጢአት ድርጊትን ማቀድ አለበት፡፡ ፈተና የፈለገውን ያህል ጠንካራ ቢሆንም ኃጢአት ለመስራት ምክንያት መሆን አይችልም፡፡ «የእግዚአብሔር ዓይኖች በቅዱሳን ላይ ናቸው፣ ጆሮዎቹም ፀሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፡፡» የተፈተንክ ነፍስ ሆይ ወደጌታ ጩህ:: ረዳት የለሽ፣ ብቃት የሌለህ እንደ ሆንክ ራስህን በኢየሱስ ላይ ጣልና በራሱ ቃል ያዘው፡፡ ጌታ ይሰማል፡፡ የተፈጥሮ ልብ ለኃጢአት ያለውን ጠንካራ ዝንባሌ ስለሚያውቅ በእያንዳንዱ የፈተና ጊዜ ይረዳሃል፡፡ MYPAmh 50.1

በኃጢአት ወድቀሃልን? ከሆነ ሳትዘገይ ለምህረትና ይቅርታ እግዚአብሔርን ፈልገው:: አሁንም ለኃጢአተኛ ምህረት እንደተዘረጋለት ነው፡፡ በመቅበዝበዛችን ሁሉ ጌታ እየጠራን ነው፡፡ «እናንተ ወደ ኋላ ያፈገፈጋችሁ ልጆች ተመለሱ፤ እኔም ማፈግፈጋችሁን እፈውሳለሁ፡፡» Testimonies for the Church vol. 5, p177. MYPAmh 50.2