Go to full page →

በፍትወት ራስን ማዋረድ MYPAmh 49

የምግብ ፍላጎታቸውንና ፍትወታቸውን ማርካትን እንደ አብይ መልካም ሥራ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች በፍፁም መልካም ወይም እውነተኛ ታላቅ ሰዎች ሆነው አያውቁም፡፡ በዓለም አስተሳሰብ የፈለገውን ያህል ከፍ ያለ ቦታ ቢይዙም በእግዚአብሔር ግምት ዝቅ ያሉ፣ የተጠሉና የረከሱ ናቸው፡፡ እርኩሰታቸው በፊታቸው ላይ እንዲፃፍ ሰማይ አዟል፡፡ አስተሳሰባቸው ከምድር ምድራዊ ነው፡፡ ቃላቶቻቸው የአእምሮአቸውን ዝቅተኛነት ይገልፃሉ፡፡ ልባቸውን በእርኩሰት በመሙላት ከውስጡ የእግዚአብሔርን ምስል ፍቀዋል፡፡ የማገናዘብ ድምጽ ፀጥ ብሏል፤ የአእምሮ ሚዛን ተዛብቷል፡፡ ኦ የሰው ተፈጥሮ ምንኛ በፍትወት ዝቅ ብሏል! ፈቃድ ለሰይጣን አልፎ ሲሰጥ ሰዎች ምንኛ ወደ ጠለቀ እርኩሰትና ሞኝነት ይወርዱ ይሆን! እውነት ለአእምሮ በከንቱ አቤቱታ ታቀርባለች፣ ምክንያቱም ልበ ንፁህ ለሆኑ መርሆዎች ተቃዋሚ ሆኗልና፡፡ The Signs of the Times, December 1, 1881. MYPAmh 49.5