Go to full page →

የራሳችሁ አይደላችሁም MYPAmh 51

አንዳንዴ እንዲህ የሚሉ ጥያቄዎችን እንሰማለን:- «እኔ በፍጹም ደስ ያለኝን ነገር ማድረግ አልችልምን? በፍፁም የራሴን መንገድ መከተል የለብኝምን? ሁል ጊዜ ተገድቤ እኖራለሁን? በፍፁም ዝንባሌዬ በሚመራኝ መንገድ አንድን ነገር ማድረግ አልችልምን?” MYPAmh 51.1

የተፈጥሮ ዝንባሌህን መከተልን በቀነስክ ቁጥር ላንተም ሆነ ለሌሎች የተሻለ ይሆናል፡፡ የተፈጥሮ ዝንባሌዎች አቅጣጫን ስተዋል፤ የተፈጥሮ ኃይሎችም በትክክል ጥቅም ላይ አልዋሉም፡፡ ሰይጣን ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አጋጭቶታል፡፡ ያለማቋረጥ መለኮታዊውን ምስል ከሰው ለማጥፋት ይሰራል፡፡ ስለሆነም ለቃላቶቻችንና ለድርጊቶቻችን ልጓም ልናደርግላቸው ይገባል፡፡ MYPAmh 51.2