Go to full page →

ግምትን መቆጣጠር MYPAmh 55

አስተሳሰብሽን መቆጣጠር አለብሽ፡፡ ይህ ግን ቀላል ሥራ አይሆንልሽም፡፡ የቅርብ ክትትልና ከፍተኛ ጥረት ሳይደረግ ሊፈፀም አይችልም፡፡ ሆኖም አምላክ ካንቺ ይህን ይሻል፡፡ ተጠያቂነት ባለው በእያንዳንዱ ፍጡር ላይ የሚያርፍ ተግባር ነው፡፡ ለምታስቢያቸው ሃሳቦችሽ በእግዚአብሔር ፊት ሃላፊነት አለብሽ፡፡ አእምሮሽ ንፁህ ባልሆኑ ነገሮች እንዲጠመድ በመፍቀድ ከንቱ የሆኑ አስተሳሰቦችን ብታስተናግጂ በእግዚአብሔር ፊት ሐሳብሽን በተግባር የፈፀምሽ ያህል በደለኛ ነሽ፡፡ ወደ ተግባር እንዳይለወጥ የከለከለው እድሉን አለማግኘት ብቻ ነው፡፡ MYPAmh 55.4

ቀንና ማታ ማለምና ግንብ መገንባት አደገኛና መጥፎ ልምድ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ልምዶች አንዴ ሥር ከሰደዱ በኋላ ከእነርሱ መላቀቅና ሐሳቦችን ወደ ንፁህ፣ ቅዱስና ከፍ ያሉ ግቦች መምራት አዳጋች ነው፡፡ አእምሮሽን መቆጣጠርና ከንቱና የሚያረክሱ ሐሳቦች ነፍስሽን እንዳያጎድፉ ከፈለግሽ በዓይኖችሽ፣ በጆሮዎችሽና በመላው የስሜት ህዋሳቶችሽ ላይ ታማኝ ዘብ መሆን አለብሽ፡፡ ይህን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ሥራ መፈፀም የሚችለው የፀጋ ኃይል ብቻ ነው፡፡ በዚህ አቅጣጫ አንቺ ደካማ ነሽ፡፡ MYPAmh 55.5