Go to full page →

ለፍላጎትዋ ለተገዛች ሴት ልጅ የተሰጠ ምክር MYPAmh 55

በሰማይ ንጉስና ቁጥር ስፍር በሌላቸው ንፁህ የሰማይ መላእክት ፊት የተገለጠ ያለፈው ዓመት አስፈሪ መዝገብ አለሽ፡፡ ሐሳቦችሽና ድርጊቶችሽ •እንደዚሁም ያልተቀደሱ ፍላጎቶችሽ ከሟቾች ተደብቀው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እጅግ ተራ የሆኑ የሕይወትሽ ድርጊቶች ለእግዚአብሔር እይታ ክፍት ናቸው፡፡ በሰማይ የጎደፈ መዝገብ አለሽ:: የፈፀምሻቸው ኃጢአቶች በሙሉ እዚያ ተመዝግበዋል፡፡ MYPAmh 55.1

የእግዚአብሔር ፊት የተፈታልሽ አይደለሽም፤ ሆኖም ስሜት የሌለሽ ትመስያለሽ፡፡ ተስፋ በሌለው ሁኔታ መጥፋትሽን አልተገነዘብሽም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፀፀት ስሜት አለሽ ፤ ነገር ግን ኩሩና በራስ መተማመን የተሞላ መንፈስሽ ወዲያውኑ ከፀፀትሽ በላይ ይነሳና የህሊና ድምጽን ( ወቀሳን) ታፍኝያለሽ፡፡ MYPAmh 55.2

ደስተኛ አይደለሽም፡፤ ነገር ግን ያለ አንዳች ገደብ የራስሽን መንገድ እንድትከተዪ ብትተዪ ደስተኛ እንደምትሆኚ ትገምችያለሽ፡፡ ምስኪን ልጅ! አንቺ ሄዋን በኤድን ገነት ይዛ የነበረውን ቦታ ነው ይዘሽ ያለሽው፡፡ እግዚአብሔር እንዳይሞቱ በማለት እንዳይነኩ የከለከለውን ፍሬ ብትበላ እጅግ ከፍ ከፍ እንደምትል ገመተች፡፡ ፍሬውን በላች፤ የኤድንን ክብር በሙሉ አጣች፡፡ MYPAmh 55.3