Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ግምትን መቆጣጠር

    አስተሳሰብሽን መቆጣጠር አለብሽ፡፡ ይህ ግን ቀላል ሥራ አይሆንልሽም፡፡ የቅርብ ክትትልና ከፍተኛ ጥረት ሳይደረግ ሊፈፀም አይችልም፡፡ ሆኖም አምላክ ካንቺ ይህን ይሻል፡፡ ተጠያቂነት ባለው በእያንዳንዱ ፍጡር ላይ የሚያርፍ ተግባር ነው፡፡ ለምታስቢያቸው ሃሳቦችሽ በእግዚአብሔር ፊት ሃላፊነት አለብሽ፡፡ አእምሮሽ ንፁህ ባልሆኑ ነገሮች እንዲጠመድ በመፍቀድ ከንቱ የሆኑ አስተሳሰቦችን ብታስተናግጂ በእግዚአብሔር ፊት ሐሳብሽን በተግባር የፈፀምሽ ያህል በደለኛ ነሽ፡፡ ወደ ተግባር እንዳይለወጥ የከለከለው እድሉን አለማግኘት ብቻ ነው፡፡MYPAmh 55.4

    ቀንና ማታ ማለምና ግንብ መገንባት አደገኛና መጥፎ ልምድ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ልምዶች አንዴ ሥር ከሰደዱ በኋላ ከእነርሱ መላቀቅና ሐሳቦችን ወደ ንፁህ፣ ቅዱስና ከፍ ያሉ ግቦች መምራት አዳጋች ነው፡፡ አእምሮሽን መቆጣጠርና ከንቱና የሚያረክሱ ሐሳቦች ነፍስሽን እንዳያጎድፉ ከፈለግሽ በዓይኖችሽ፣ በጆሮዎችሽና በመላው የስሜት ህዋሳቶችሽ ላይ ታማኝ ዘብ መሆን አለብሽ፡፡ ይህን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ሥራ መፈፀም የሚችለው የፀጋ ኃይል ብቻ ነው፡፡ በዚህ አቅጣጫ አንቺ ደካማ ነሽ፡፡MYPAmh 55.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents