Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በእውነት ላይ መጠራጠርን በተመለከተ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

    ስለ ወጣቶቻችን እጅግ የጠለቀ ሃዘን ይሰማኛል፡፡ አደጋውን እንደ ማወቄ ካገኛችሁት ጥቂት የሳይንስ እውቀት የተነሳ ራሳችሁ በሰይጣን ወጥመድ እንዳትጠመዱ አስጠነቅቃችኋለሁ፡፡ ያለ ፈርሃ-እግዚአብሔር ልታገኘው ከምትችለው እውቀት ሁሉ ይልቅ ንፁህና ትሁት ልብ ያለህ መሆን ይሻላል፡፡MYPAmh 61.1

    የዛሬ ወጣቶች የትም ቢሄዱ ተጠራጣሪዎችንና አረመኔዎችን የመገናኘት አጋጣሚ ስላላቸው ስለሚያምኑት ተስፋ በገርነትና በፍርሃት ማብራሪያ መስጠት እንዲችሉ በበቂ ሁኔታ የታጠቁ መሆን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ቶማስ ፔይን ሞቶ በመቃብር ውስጥ ያለ ቢሆንም ሥራዎቹ በዓለም •ርግማን ሆነው ይኖራሉ፡፡ ዛሬም የእግዚአብሔርን ቃል እውነት የሚጠራጠሩ፣ እነዚህን የአረመኔነት ውጤቶችን ልምድ በሌላቸው ወጣቶች እጅ በማስቀመጥ ልባቸውን መርዘኛ በሆነ የጥርጣሬ ከባቢ አየር ይሞላሉ፡፡ የሰይጣን መንፈስ ነፍሳትን የማጥፋት ስልቱን ለማሳካት በክፉ ሰዎች ውስጥ ይሰራል፡፡MYPAmh 61.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents