Go to full page →

ታማኝ ጓደኛ MYPAmh 18

ክርስቶስ ወደ አባቱ ባረገ ጊዜ ተከታዮቹን ያለእርዳታ አልተዋቸውም:: እጅግ ብዙ ከሆኑ የእምነት ጠላቶች ጋር መልካሙን የእምነት ገድል የሚጋደሉትን እንዲረዳ መንፈስ ቅዱስ እንደየሱስ ወኪልና ቅዱሳን መላእክት እንደአገልጋይ መናፍስት ተልከው ነበር:: ሁልጊዜ የሱስ ረዳትህ እንደሆነ አስብ:: ልዩ ባህሪይህን እንደእርሱ የሚያስተውል ማንም የለም:: በእርሱ ለመመራት ፈቃደኛ ከሆንክ ላንተ ያለውን ፈቃዱን እንድትፈጽም የሚያስችልህን መልካም ተጽእኖዎች በዙሪያህ ለማሰለፍ እየተጠባበቀ ነው:: MYPAmh 18.7

በዚህ ህይወት ለወደፊቱ ህይወት እየተዘጋጀን ነን፤ እያንዳንዱ ፍፁም ባህሪይን ለማጎልበት የሚፈልግ ነፍስ ህይወትን የሚመረምረውን የእግዚአብሔርን ፈተና የሚቀበልበት ታላቅ ምርመራ በቶሎ ሊሆን ነው:: ሌሎች ያለአንዳች አደጋ ሊከተሉት የሚችሉትን ምሳሌ በፊታቸው አስቀምጠሃል ወይ? በተጠየቅክ ጊዜ ተገቢ መልስ መስጠት እንደሚያስችልህ ሆነህ ለነፍሳት ተጠንቅቀሃል ወይ? የሰማይ ሰራዊት በወጣቶች ላይ ፍላጎት አላቸው:: ፈተናውን አልፋችሁ « አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂት ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ እነሆ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ::» የሚል ማረጋገጫ ሲሰጥ ለመስማት ታላቅ ጉጉት አላቸው:: MYPAmh 19.1

ወጣቶች ዘላለማዊ ባህርይን እዚህ መገንባት እንዳለባቸውና የሚቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ እግዚአብሔር እንደሚፈልግባቸው ያስታውሱ:: ታላላቆች ለታናናሾች ይጠንቀቁ:: ፈተና ደርሶባቸው ሲያዩ ለብቻቸው ይውሰዱአቸውና ይፀልዩላቸው፤ አብረውም ይፀልዩ:: የሱስ ሊያድናቸው ለመጣላቸው ነፍሳት ፍላጎት ሲኖረን እግዚአብሔር እንደታላቅ መስዋዕትነት ይመለከተዋል:: ወጣቶች ክርስቶስን ቢሹ ኖሮ ጌታ ጥረታቸውን ውጤታማ ያደርገው ነበር:: E.G.White, The Youth’s Instructor, November 21, 1911. MYPAmh 19.2