Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ታማኝ ጓደኛ

    ክርስቶስ ወደ አባቱ ባረገ ጊዜ ተከታዮቹን ያለእርዳታ አልተዋቸውም:: እጅግ ብዙ ከሆኑ የእምነት ጠላቶች ጋር መልካሙን የእምነት ገድል የሚጋደሉትን እንዲረዳ መንፈስ ቅዱስ እንደየሱስ ወኪልና ቅዱሳን መላእክት እንደአገልጋይ መናፍስት ተልከው ነበር:: ሁልጊዜ የሱስ ረዳትህ እንደሆነ አስብ:: ልዩ ባህሪይህን እንደእርሱ የሚያስተውል ማንም የለም:: በእርሱ ለመመራት ፈቃደኛ ከሆንክ ላንተ ያለውን ፈቃዱን እንድትፈጽም የሚያስችልህን መልካም ተጽእኖዎች በዙሪያህ ለማሰለፍ እየተጠባበቀ ነው::MYPAmh 18.7

    በዚህ ህይወት ለወደፊቱ ህይወት እየተዘጋጀን ነን፤ እያንዳንዱ ፍፁም ባህሪይን ለማጎልበት የሚፈልግ ነፍስ ህይወትን የሚመረምረውን የእግዚአብሔርን ፈተና የሚቀበልበት ታላቅ ምርመራ በቶሎ ሊሆን ነው:: ሌሎች ያለአንዳች አደጋ ሊከተሉት የሚችሉትን ምሳሌ በፊታቸው አስቀምጠሃል ወይ? በተጠየቅክ ጊዜ ተገቢ መልስ መስጠት እንደሚያስችልህ ሆነህ ለነፍሳት ተጠንቅቀሃል ወይ? የሰማይ ሰራዊት በወጣቶች ላይ ፍላጎት አላቸው:: ፈተናውን አልፋችሁ « አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂት ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ እነሆ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ::» የሚል ማረጋገጫ ሲሰጥ ለመስማት ታላቅ ጉጉት አላቸው::MYPAmh 19.1

    ወጣቶች ዘላለማዊ ባህርይን እዚህ መገንባት እንዳለባቸውና የሚቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ እግዚአብሔር እንደሚፈልግባቸው ያስታውሱ:: ታላላቆች ለታናናሾች ይጠንቀቁ:: ፈተና ደርሶባቸው ሲያዩ ለብቻቸው ይውሰዱአቸውና ይፀልዩላቸው፤ አብረውም ይፀልዩ:: የሱስ ሊያድናቸው ለመጣላቸው ነፍሳት ፍላጎት ሲኖረን እግዚአብሔር እንደታላቅ መስዋዕትነት ይመለከተዋል:: ወጣቶች ክርስቶስን ቢሹ ኖሮ ጌታ ጥረታቸውን ውጤታማ ያደርገው ነበር:: E.G.White, The Youth’s Instructor, November 21, 1911.MYPAmh 19.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents