Go to full page →

ትእዛዞቹ ሥልጣን ሰጮችም ናቸው፡፡ MYPAmh 69

በተግባር ወደ ፍጽምና የሚደርሰውን ባሕሪይን ፍፁም ለማድረግ በጽኑ እምነት ከሚሻ ሰብዓዊ ወኪል ጋር የሰማይ አካላት ይሠራሉ፡፡ በዚህ ሥራ ላይ ለተሰማራ ለእያንዳንዱ ግለሰብ ክርስቶስ እኔ ልረዳህ በቀኝ እጅህ በኩል ነኝ ይላል፡፡ MYPAmh 69.1

የሰው ፈቃድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ሲተባበር ሁሉን የሚችል ይሆናል፡፡ በእርሱ ትዕዛዝ የሚፈጸም ነገር ሁሉ በእርሱ ብርታት ይፈፀማል፡፡ የእርሱ ትዕዛዞች በሙሉ ሥልጣን ሰጮችም ናቸው፡፡ Christ’s Object Lessons, p. 331-333. MYPAmh 69.2