Go to full page →

የሁልጊዜ መደገፊያችን MYPAmh 69

ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር መደገፍን የማይገነዘቡ በፈተና ይሸነፋሉ፡፡ እግሮቻችን በአስተማማኝ ሁኔታ እንደ ቆሙና በፍጹም እንደማንናወጥ ሊሰማን ይችላል፡፡ በመተማመን «በማን እንዳመንኩ አውቃለሁ፤ በእግዚአብሔርና በቃሉ ያለኝን እምነት ምንም ነገር ሊያናውጥ አይችልም” ልንል እንችላለን፡፡ ነገር ግን ሰይጣን በውርስና በልምድ ያገኘናቸውን የባሕሪይ መገለጫዎች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዓይኖቻችን ለጉድለቶቻችንና ለፍላጎቶቻችን እንዲታወሩ እያቀደ ነው፡፡ በደህንነት መሄድ የምንችለው ድክመታችንን በመገንዘብና ሁል ጊዜ ወደ ክርስቶስ በመመልከት ብቻ ነው፡፡ The Desire of Ages, p. 382. MYPAmh 69.3