Go to full page →

የአስተሳሰብ ልምዳችንን መቀየር MYPAmh 76

በራሳቸው በኩል ልባዊ ጥረትን ሳያደርጉ የእግዚአብሔርን የፍቅር ዋስትና እናገኛለን ብለው ማናቸውም አያስቡ። አእምሮ በምድራዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ሲደረግ የአስተሳሰብ ልምድን መቀየር ከባድ ነገር ይሆናል:: ዓይን የሚያየውና ጆሮ የሚሰማው ብዙ ጊዜ ትኩረትን ይስባል፤ ፍላጎትንም ይመስጣል። MYPAmh 76.3

ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ከተማ የምንገባና ኢየሱስን በክብሩ የምናይ ከሆነ አሁን እርሱን እዚሁ በእምነት ዓይን መመልከትን መለማመድ አለብን። የኢየሱስ ቃላትና ባሕሪዩ አብዛኛውን ጊዜ የአስተሳሰባችንና የንግግራችን ርዕስ መሆን አለበት። በየዕለቱ የተወሰነ ሰዓት በተለየ ሁኔታ በእነዚህ ቅዱስ ዓለማዎች ላይ በፀሎት ለተሞላ ማሰላሰል መሰጠት አለበት። MYPAmh 76.4