Go to full page →

ክፍል 4—በብርሃን መጓዝ MYPAmh 81

አዳኙ በደሙ ወደ ገዛቸው በማዘንበል ሊገለፅ በማይችል ፍቅርና ርህራሄ “ሙሉ መሆን ትፈልጋላችሁን?” እያለ ነው። በጤንነትና ሰላም እንድትነሱ ይጠይቃችኋል። ሙሉ መሆናችሁ እስኪሰማችሁ ድረስ አትጠብቁ። በአዳኙ ቃል እምነት ይኑራችሁ። ፈቃዳችሁን በክርስቶስ በኩል አድርጉ። ለማገልገል ፈቃደኛ ሁኑ፡ ቃሉ ያዘዛችሁን በመተግበር ብርታት ታገኛላችሁ:: ከማንኛውም ክፉ ልምምድ ማለትም ለረጅም ጊዜ ከመፈፀማችሁ የተነሣ ነፍሳችሁንና አካለችሁን አስሮ ጌታ ከሆነው ፍላጎት ክርስቶስ ነፃ ሊያወጣችሁ ይችላል:: በጉጉትም እየጠበቀ ነው። “በኃጢአት ለሞተች” ነፍስ ሕይወት ይሰጣታል። በድካም፣ በመጥፎ ልምድና፣ በኃጢአት ሰንሰለት ተይዞ ያለውን ምርኮኛ ነፃ ያወጠዋል። The Ministry of Healing P.84, 85. MYPAmh 81.1