Go to full page →

ሕያው ልምምድ MYPAmh 92

እግዚአብሔር በክርስቶስ ሥጦታ ከራሱ ጋር ሊያገናኘን እንዲሚችል ለማሳየት የክብር ጌታ መለኮታዊነቱን በሰብዓዊነት ሸፈነው። የወደቀው ሰብአዊ ዘር ሰማያዊ አባታችን በፍቅሩ ተናዛዡን ኃጢአተኛ ነውር በሌለው የእግዚአብሔር በግ መልካም ሥራ ለውጦ አቅፎት ካልያዘው በቀር እንደማይረካ ማወቅ አለበት። MYPAmh 92.1

የሰማያዊ ኃይላት ሥራ መጨረሻ ግባቸው ይህ ነው። በመተላለፋቸው ምክንያት ከሰማያዊ አባታቸው የተለዩትን መልሰው ለማምጣት በጄኔራላቸው ትዕዛዝ ይሠራሉ። አስደናቂው የክርስቶስ ፀጋና ፍቅር ለዓለም የሚገለጥበት እቅድ ተዘጋጀ። ይህ በፀጋ የተሞላው የደህንነት ዕቅድ ዓለምን ለማዳን በቂ ነው። ኃጢአተኛውና የወደቀው ሰው በኃጢአት ይቅርታና በተቆጠረለት የክርስቶስ ፅድቅ አማካይነት በኢየሱስ ሙሉ ይሆናል። MYPAmh 92.2