Go to full page →

ሰፊ አስተሳሰብ ይኑርህ MYPAmh 23

ወጣቶች የተሰጡአቸውን እድሎች ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንዲችሉ ራዕይ እንዲኖራቸውና ሐዋርያትን ያነሳሳው ድፍረት እንዲኖራቸው ሰፊ አስተሳሰብና በጥበብ የታቀዱ እቅዶች ሊኖሩአቸው ይገባል:: ዮሐንስ « ወጣቶች ሆይ ብርቱ ስለሆናችሁና የእግዚአብሔር ቃል በውስጣችሁ ስለሚኖር ጽፌላችኋለሁ:: ክፉውንም አሸንፋችኋል” ይላል:: በወጣቶች ፊት ከፍ ያለ መስፈርት ተቀምጧል:: ለእርሱ እውነተኛ አገልግሎት እንዲሰጡ እግዚአብሔር እየጋበዛቸው ነው:: እውነተኛ ልብ ያላቸውና በክርስቶስ ት/ቤት መማር የሚፈልጉ ወጣቶች በዘመናት ሁሉ እስከኛ ጊዜ ድረስ «ሰው ሁን፣በርታ::» እያለ የሚያስተጋባውን የጦር መሪ ትዕዛዝ ቢሰሙ ለጌታ ታላቅ ሥራ መስራት ይችላሉ:: MYPAmh 23.4

ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና የምትሄዱ” እርሱ በሰጣችሁ ወንድነት በፊቱ የምትቆሙ፣ ከእርኩሰት የነፃችሁ፣ ዘመኑን እያረከሰ ካለው ፍትወታዊ ብክለት ነፃ የምትሆኑ ወንዶች መሆን አለባችሁ:: ስህተትንም ሆነ ኃጢአተኝነትን የምትጠሉ” በደም የቀለመውን የልዑል አማኑኤልን ባንዲራ ከፍ አድርጋችሁ በመያዝ እውነተኛና ጀግና ለመሆን የምትደፍሩ ወንዶች መሆን አለባችሁ:: መክሊቶቻችሁን ለጌታ በተጠቀማችሁ መጠን ይጨመሩና ስፍር በሌለው ዋጋ እጅግ የከበሩ ሆነው ይቆጠራሉ:: አንድ ትልቅ ነገር ለማድረግ ስለማትችሉ ብቻ ምንም ነገር ላለማድረግ ቁጭ አትበሉ:: ነገር ግን እጆቻችሁ ለመስራት ያገኙትን ሁሉ በሙሉ ልብና በኃይል ሥሩ……..:: MYPAmh 23.5