Go to full page →

ለምልመላ ጥሪ MYPAmh 23

ክርስቶስ ፈቃደኞችን ከ•ርሱ ዓላማ ሥር እንዲመዘገቡና የመስቀልን ዓላማ እንዲሸከሙ እየጠራቸው ነው:: ቤተክርስቲያን በድፍረት የተሞላ ምስክርነትን የሚሸከሙ፣ ባላቸው የጋለ ቅንዓት የዛለውን የእግዚአብሔር ህዝብ ኃይል የሚቀሰቅሱና የቤተክርስቲያንን ኃይል በዓለም ላይ የሚጨምሩ ወጣት ወንዶችን በማጣት እየደከመች ነው:: የአለማዊነትን ማዕበል የሚከላከሉና በፍትወትና በእርኩሰት ላይ የመጀመሪያ እርምጃ በመውሰድ የተቃውሞ ድምፅ የሚያነሱ ወጣት ወንዶች ይፈለጋሉ:: MYPAmh 23.6

ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያገለግሉና ራሳቸውን ለሥራው የሚሰጡ ወጣቶች በመጀመሪያ የነፍስን ቤተመቅደስ ከእርኩሰት ሁሉ ማጽዳትና ክርስቶስን በልባቸው ማንገስ አለባቸው:: ከዚያ በኋላ በክርስቲያናዊ ጥረታቸው ኃይል እንዲጨምሩ ይደረጉና ሰዎች ከክርስቶስ ጋር እንዲታረቁ ለማድረግ የጋለ ቅንዓት ያሳያሉ:: ወጣቶቻችን ለክርስቶስ ጥሪ «እነሆ እኔን ላክ» ብለው አይመልሱለትምን? ወጣቶች ሆይ! ወደፊት እየገፋችሁና ሥራውን እርሱ ካቆመበት በመቀበል እስከፍፃሜው በመሸከም ከክርስቶስ ጋር አብሮ ሠራተኛ መሆናችሁን አሳዩ:: Review and Herald, June16, 1891. MYPAmh 24.1