Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሰፊ አስተሳሰብ ይኑርህ

    ወጣቶች የተሰጡአቸውን እድሎች ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንዲችሉ ራዕይ እንዲኖራቸውና ሐዋርያትን ያነሳሳው ድፍረት እንዲኖራቸው ሰፊ አስተሳሰብና በጥበብ የታቀዱ እቅዶች ሊኖሩአቸው ይገባል:: ዮሐንስ « ወጣቶች ሆይ ብርቱ ስለሆናችሁና የእግዚአብሔር ቃል በውስጣችሁ ስለሚኖር ጽፌላችኋለሁ:: ክፉውንም አሸንፋችኋል” ይላል:: በወጣቶች ፊት ከፍ ያለ መስፈርት ተቀምጧል:: ለእርሱ እውነተኛ አገልግሎት እንዲሰጡ እግዚአብሔር እየጋበዛቸው ነው:: እውነተኛ ልብ ያላቸውና በክርስቶስ ት/ቤት መማር የሚፈልጉ ወጣቶች በዘመናት ሁሉ እስከኛ ጊዜ ድረስ «ሰው ሁን፣በርታ::» እያለ የሚያስተጋባውን የጦር መሪ ትዕዛዝ ቢሰሙ ለጌታ ታላቅ ሥራ መስራት ይችላሉ::MYPAmh 23.4

    ከእግዚአብሔር ጋር በትህትና የምትሄዱ” እርሱ በሰጣችሁ ወንድነት በፊቱ የምትቆሙ፣ ከእርኩሰት የነፃችሁ፣ ዘመኑን እያረከሰ ካለው ፍትወታዊ ብክለት ነፃ የምትሆኑ ወንዶች መሆን አለባችሁ:: ስህተትንም ሆነ ኃጢአተኝነትን የምትጠሉ” በደም የቀለመውን የልዑል አማኑኤልን ባንዲራ ከፍ አድርጋችሁ በመያዝ እውነተኛና ጀግና ለመሆን የምትደፍሩ ወንዶች መሆን አለባችሁ:: መክሊቶቻችሁን ለጌታ በተጠቀማችሁ መጠን ይጨመሩና ስፍር በሌለው ዋጋ እጅግ የከበሩ ሆነው ይቆጠራሉ:: አንድ ትልቅ ነገር ለማድረግ ስለማትችሉ ብቻ ምንም ነገር ላለማድረግ ቁጭ አትበሉ:: ነገር ግን እጆቻችሁ ለመስራት ያገኙትን ሁሉ በሙሉ ልብና በኃይል ሥሩ……..::MYPAmh 23.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents