Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ትኩረት የመስጠት ጠቀሜታ

    በእጃችን ባለው ሥራ ላይ የማተኮር ችሎታ ታላቅ በረከት ነው። እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወጣቶች አስተሳሰባቸውን በትክክለኛው መስመር በመጠበቅና የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ኃላፊነቶቻቸውን (የተሰጣቸውን ሥራ) ትኩረት በመስጠት ለመፈፀም መጣር አለባቸው። አሁን በእጃቸው ያሉትን ተግባራት መገንዘብና አእምሮአቸው እንዲባዝን ባለመፍቀድ መፈፀም አለባቸው። አእምሮን በዚህ መልክ ማሰልጠን በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ይጠቅማቸዋል። በሚያደርጉት በእያንዳንዱ ነገር ላይ ተገቢ የሆነ ትኩረት መስጠትን የሚማሩ ሥራው ምንም ያህል ትንሽ ቢመስልም በዓለም ላይ ጠቃሚ ሰዎች ይሆናሉ።MYPAmh 99.2

    ውድ ወጣቶች! የምትተጉና የማትደክሙ ሁኑ። “የአእምሮአችሁን ወገብ ታጠቁ።” በልቡ ለእግዚአብሔር እውነተኛ ለመሆን እንደ ወሰነው እንደ ታማኙ ዕብራዊ ዳንኤል ቁሙ። ወላጆቻችሁንና ጓደኞቻችሁን ተስፋ አታስቆርጡአቸው። ሌላም ማስታወስ የሚገባችሁ ነገር አለ። ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ሠራተኛ መሆን እንድትችሉ ለማድረግ ሕይወቱን እስከ መስጠት ድረስ የወደዳችሁን ጌታ አታሳዝኑት።MYPAmh 99.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents