Go to full page →

በውስጥ የሚኖር ደስታ MYPAmh 99

ወደ ዘላላማዊ ሕይወት በሚወስደው አቀበታማ መንገድ ላይ የደከሙትን የሚያድሱ የደስታ ምንጮች አሉ። በጥበብ መንገድ የሚሄዱ ሰዎች በመከራ ውስጥም ቢሆኑ ነፍሳቸው የምትወደው ጌታቸው ሳይታይ በአጠገባቸው ስለሚሄድ እጅግ ደስተኞች ናቸው። በእያንዳንዱ ወደ ላይ በሚያደርጉት እርምጃ የእርሱን እጅ ንካት በግልፅ ያዩታል። በእያንዳንዱ እርምጃ ከማይታየው አምላክ ብሩህ ነፀብራቆች በመንገዳቸው ላይ ያርፋሉ። የምሥጋና መዝሙሮቻቸውም ወደ ላይ ከፍ ባለ ጣዕመ ዜማ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ካሉ መላእክት መዝሙር ጋር በመቀላቀል ወደ ላይ ይወጣሉ።—Thoughts From the Mount of Blessing, 140 MYPAmh 99.6