Go to full page →

የክንውን መስፈርቶች (መለኪያዎች) MYPAmh 26

“የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው::” አብዛኛዎቹ ወጣቶቻችን የሚችሉትን ሁሉ በሁሉም ጊዜያቶችና በማንኛውም ሁኔታ ለማድረግ ኃይሎቻቸውን ለብርቱ ሥራ ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ አይሰማቸውም:: በአይኖቻቸው ፊት ፈርሐ እግዚአብሔር የለም:: ሐሳቦቻቸውም ንፁህና የከበሩ አይደሉም:: MYPAmh 26.1

ሰማይ በሞላ እያንዳንዱን ሐሳብና ድርጊት ያውቃል:: ድርጊቶችህ አብረውህ ከሚሆኑት ሰዎች የተሰወሩ ሊሆኑ ይችላሉ:: ነገር ግን ለመላእክት እይታ ክፍት ናቸው:: እያንዳንዱን መጥፎ ልምድ ለማሸነፍና ከሰይጣን የማታለያ ወጥመዶች ነፃ ሆነው ለመቆም የሚፈልጉትን ለማገልገል መላእክት ይላካሉ:: MYPAmh 26.2