Go to full page →

የክርስቲያን ትምህርት አስፈላጊነት MYPAmh 114

እግዚአብሔር የአእምሮ ችሎታዎችን እንድናሰለጥን ይፈልግብናል፡፡ አገልጋዮቹ ከዓለማውያን ይልቅ የበለጠ እውቀትና የጠራ ችሎታ እንዲኖራቸው መንገድ ያዘጋጃል፡፡ ብቁና በቂ እውቀት ያላቸው ሰራተኞች ለመሆን ቸልተኛና ሰነፍ በሆኑት አይደሰትም፡፡ ጌታ በሙሉ ልባችን፣ በሙሉ ነፍሳችን፣ በሙሉ ኃይላችንና በሙሉ አእምሮአችን እንድንወደው ይጠይቀናል፡፡ MYPAmh 114.1

ይህ በሙሉ አእምሮአችን ፈጣሪያችንን እንድናውቅና እንድንወደው፣ የአእምሮ ችሎታችንን እስከ ሙላት ድረስ እንድናሳድግ ግዴታ ያስቀምጥልናል፡፡ አእምሮአችንን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር በማድረግ የበለጠ ባሰለጠንነው መጠን በብቃት በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ መዋል ይችላል፡፡ ያልተማረ ሰው ሆኖ ለእግዚአብሔር ራሱን የቀደሰና ሌሎችን ለመባረክ የሚጓጓን ሰው ጌታ በአገልግሎቱ ውስጥ ሊጠቀመው ይችላል፣ ይጠቀምበታልም፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ የሆነ ራስን ለእግዚአብሔር ቀድሶ የመስጠት መንፈስ ያላቸውና በቂ የሆነ ትምህርት የማግኘት እድሉ የነበራቸው ሰዎች ካልተማሩት እጅግ የበለጠ ሥራ ለክርስቶስ መሥራት ይችላሉ፡፡ እነርሱ በተሸለ ቦታ ቆመዋል፡፡ MYPAmh 114.2