Go to full page →

ለከፍተኛ አገልግሎት መሰልጠን MYPAmh 114

እውቀታችንን ለሌሎች የመጋራትን አላማ በፊታችን አድርገን ልንደርስበት የምንችለውን እውቀት ሁሉ እንድናገኝ ጌታ ይሻል፡፡ ለእግዚአብሔር ለመስራትም ሆነ ለመናገር መቼ ወይንም የት እንደሚጠራ ማወቅ የሚችል ማንም የለም፡፡ ሰዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚችል የሚያወቅ ሰማያዊ አባቻችን ብቻ ነው፡፡ ደካማ እምነታችን ለይቶ ለማወቅ የማይችላቸው አጋጣሚዎች በፊታችን ናቸው፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የእግዚአብሔርን ስም ለማስከበር የቃሉን እውነቶች እጅግ ከፍተኛ በሆኑ ምድራዊ ባለስልጣናት ፊት እንኳን ለማቅረብ አእምሮአችንን ማሰልጠን አለብን፡፡ ለእግዚአብሔር ለመስራት አእምሮአችንን በትምህርት ብቁ የማድረግ አንዲት አጋጣሚ እንኳን እንድታመልጠን መፍቀድ የለብንም፡፡ MYPAmh 114.3