Go to full page →

ፍፁም መቀደስ MYPAmh 26

ዓለም ለአሁኑም ሆነ ለወደፊት ጥቅም የምትቆሙበትን ቦታ ማወቅ እንዲችል ራሳችሁን ሙሉ በሙሉ ለትክክለኛ ነገር አሳልፋችሁ ስጡ:: ብዙዎች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሥራ አሳልፈው ያልሰጡ ስለሆኑ የእነርሱ ማመንታት በራሱ የድካም ምንጭና ለሌሎች የመሰናከያ አለት ነው:: የተረጋጋ መርህ ሳይኖራቸውው፣ ሳይቀደሱ እያሉ እነርሱ ትክክል ነው ብለው ከሚያምኑት ነገር የፈተና ማዕበሎችበመምጣት ይጠራርጓቸዋል:: እያንዳንዱን ስህተት በተቆጠረላቸው የክርስቶስ ጽድቅ አማካይነት ለማሸነፍና ቅዱስ ባህሪይን ለመመስረት ጥረት አያደርጉም:: MYPAmh 26.6

ከእያንዳንዱ አስተዋይ ከሆነ ሰብዓዊ ፍጡር ምን እንደሚጠበቅ ዓለም የማወቅ መብት አለው:: የፅኑ፣ ጠንካራ፣ ቅዱስ መርሆዎች ህያው መኖሪያ የሆነ ሰው በጓደኞቹ ላይ ህያው ኃይል ይሆናል:: በክርስትናው በሌሎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል:: እያንዳንዱ ግለሰብ ለክፉ ወይም ለመልካም ያለው ተጽእኖ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ብዙዎች ተገንዝበው አያደንቁትም:: እያንዳንዱ ተማሪ የሚከተለው መርህ በባህርይ ላይ ህያውና መቅረጽ የሚችል ተጽእኖ እንዳለው መረዳት አለበት:: ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለ ሰው ኢየሱስንና ክርስቶስ የሞተላቸውን ሁሉ ይወዳል:: ክርስቶስ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ህይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል:: ራሱን ያለ አንዳች መቆጠብ ለክርስቶስ አገዛዝ አሳልፎ ይሰጣል:: MYPAmh 27.1