Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ፍፁም መቀደስ

    ዓለም ለአሁኑም ሆነ ለወደፊት ጥቅም የምትቆሙበትን ቦታ ማወቅ እንዲችል ራሳችሁን ሙሉ በሙሉ ለትክክለኛ ነገር አሳልፋችሁ ስጡ:: ብዙዎች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሥራ አሳልፈው ያልሰጡ ስለሆኑ የእነርሱ ማመንታት በራሱ የድካም ምንጭና ለሌሎች የመሰናከያ አለት ነው:: የተረጋጋ መርህ ሳይኖራቸውው፣ ሳይቀደሱ እያሉ እነርሱ ትክክል ነው ብለው ከሚያምኑት ነገር የፈተና ማዕበሎችበመምጣት ይጠራርጓቸዋል:: እያንዳንዱን ስህተት በተቆጠረላቸው የክርስቶስ ጽድቅ አማካይነት ለማሸነፍና ቅዱስ ባህሪይን ለመመስረት ጥረት አያደርጉም::MYPAmh 26.6

    ከእያንዳንዱ አስተዋይ ከሆነ ሰብዓዊ ፍጡር ምን እንደሚጠበቅ ዓለም የማወቅ መብት አለው:: የፅኑ፣ ጠንካራ፣ ቅዱስ መርሆዎች ህያው መኖሪያ የሆነ ሰው በጓደኞቹ ላይ ህያው ኃይል ይሆናል:: በክርስትናው በሌሎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል:: እያንዳንዱ ግለሰብ ለክፉ ወይም ለመልካም ያለው ተጽእኖ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ብዙዎች ተገንዝበው አያደንቁትም:: እያንዳንዱ ተማሪ የሚከተለው መርህ በባህርይ ላይ ህያውና መቅረጽ የሚችል ተጽእኖ እንዳለው መረዳት አለበት:: ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለ ሰው ኢየሱስንና ክርስቶስ የሞተላቸውን ሁሉ ይወዳል:: ክርስቶስ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ህይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል:: ራሱን ያለ አንዳች መቆጠብ ለክርስቶስ አገዛዝ አሳልፎ ይሰጣል::MYPAmh 27.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents