Go to full page →

የሥራ ክቡርነት MYPAmh 141

በሰው አለመታዘዝ ምክንያት ወደ ዓለም የመጣውን ክፋት በሥራ አማካኝነት ለመቀነስ የእግዚአብሔር እቅድ ነበር፡፡ በሥራ አማካኝነት የሰይጣን ፈተናዎች ውጤት አልባ ይሆኑና የክፋት ማዕበል ይገታል፡፡ ምንም እንኳን ሥራ ሥጋት፣ ድካምና ህመም ያለበት ቢሆንም አሁንም የደስታና የእድገት ምንጭና ከፈተና ጠባቂያችን ነው፡፡ የሥራ መርህ በራስ ደስታ እንዳናተኩር ቁጥጥር ያደረግና ትጋትን፣ ንጽህናንና ጽናትን ያደፋፍራል፡፡ በመሆኑም ከውድቀት ለመዳን የእግዚአብሔር እቅድ ታላቅ ክፍል ይሆናል፡፡ MYPAmh 141.1