Go to full page →

የጉልበት ሥራና ስፖርታዊ ጨዋታዎች ንጽጽር MYPAmh 141

አብዛኛው ህብረተሰብ የእጅ ሥራ ክብር የሚቀንስ እንደሆነ ይሰማዋል፡፡ ነገር ግን ሰዎች የክሪኬት፣ የእግር ኳስ፣ የቤዝ ቦል ጨዋታ ወይንም የቡጢ ውድድሮችን እንደ ዝቅተኛ ነገር ሳይቆጥሩ የፈለጉትን ያህል ጉልበታቸውን ያወጣሉ፡፡ ሰይጣን ሰዎች የአካልና የአእምሮ ኃይላቸውን አስተማሪ ላልሆነ፣ ጠቃሚ ላልሆነና የእነርሱን እርዳታ ለሚፈልጉ በረከት እንዲሆኑ ለማይረዳቸው ነገር አውለውት ሲመለከት ይደሰታል፡፡ ወጣቶች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች እርግጠኛ የሆነ ጥቅም በሌላቸው የስፖርት ዓይነቶች የተዋጣላቸው ባለሙያ ሲሆኑ ሰይጣን እግዚአብሔር የሰጣቸውን መክሊቶች እየወሰደባቸውና በእነርሱ ፋንታ የራሱን የክፋት ተግባራት በማስቀመጥ በነፍሶቻቸው ላይ የህይወት ጨዋታ እየተጫወተባቸው ነው፡፡ ሰዎች እግዚአብሔርን ችላ እንዲሉ መምራት የሁል ጊዜ ጥረቱ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአስተሳሰባቸው ውስጥ ቦታ እንዳያገኝ አእምሮአቸው ሙሉ በሙሉ እንዲያዝና በሌሎች ነገሮች እንዲመሰጥ ይፈልጋል፡፡ ሰዎች የፈጣሪያቸው እውቀት እንዲኖራቸው አይፈልግም፡፡ ሰዎች በተለያዩ የእስፖርት አይነቶችና ቲያትሮች እንዲያተኩሩ በማድረግ እግዚአብሔርንና ሰማይን እንዲረሱ በማድረግ የወጣቶችን ስሜት ሲያወዛግብ እጅግ ይደሰታል፡፡ MYPAmh 141.2

ክፉን ለመከላከል እርግጠኛ ከሆኑ መጠበቂያዎች አንዱ ጠቀሜታ ያለው ሥራ ነው፡፡ ሥራ-ፈትነት ደግሞ ከታላላቆቹ እርግማኖች አንዱ ነው፡፡ ሥራ-ፈትነትን ከንቱነት፣ ወንጀልና ድህነት ይከተሉታል፡፡ ሁል ጊዜ በሥራ የተጠመዱና ወደ እለቱ ተግባሮቻቸው በደስታ የሚሄዱ ሰዎች የህብረተሰቡ ጠቃሚ አባላት ናቸው፡፡ በመንገዳቸው ላይ ያሉትን የተለያዩ ተግባራት በታማኝነት በሚፈጽሙበት ጊዜ ህይወታቸውን ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች በረከት እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ ትጋት ያለበት የጉልበት ሥራ «ሥራ-ፈት እጆች እንዲሠሩት ከሚያዘጋጅ ከአንዳንድ የማጭበርበር ተግባራት” በማራቅ ከብዙ የሰይጣን ወጥመዶች ይጠብቃቸዋል፡፡ MYPAmh 141.3

የማይፈስ ኩሬ ብዙም ሳይቆይ ይሸታል፡፡ ግን የሚፈስ ምንጭ ጤንነትንና ደስታን በምድር ላይ ያሰራጫል፡፡ አንደኛው የሥራ-ፈት ምሳሌ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የትጉህ ሠራተኛ ምሳሌ ነው…፡፡ MYPAmh 141.4