Go to full page →

የክርስቶስ ምሳሌ MYPAmh 141

ለምድር ኗሪዎች የተሰጣቸው የሥራ መንገድ ከባድና አድካሚ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የአዳኙን ዱካዎች መከተል የተከበረ ስለሆነ ይህንን የተቀደሰ መንገድ የሚከተል ሰው ከአደጋ የተጠበቀ ነው፡፡ ኢየሱስ በቃልም ሆነ በህይወት ምሳሌነቱ ጠቃሚ ለሆነ የጉልበት ሥራ ክብር ሰጥቶታል፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ የኖረው የልፋት ኑሮን ነበር፡፡ ከምድራዊ ህይወቱ አብዛኛውን ክፍል ያሳለፈው በናዝሬት በነበረው የአናፂነት ሱቅ ውስጥ በትዕግስት በመሥራት ነበር፡፡ ተራ የጉልበት ሠራተኛን ልብስ በመልበስ የሕይወት ጌታ የዚህች የኖረባትን ትንሽ ከተማ ጎዳናዎች ወደዚያ ዝቅተኛ ወደ ተባለው ሥራ ሲሄድና ሲመለስ ተራምዶበታል፡፡ እርሱ ከገበሬዎችና የጉልበት ሠረተኞች ጋር ጎን ለጎን ሳይታወቅና ተገቢ ክብር ሳይሰጠው ሲራመድ ሳለ አገልጋይ መላእክት ይከተሉት ነበር…፡፡ MYPAmh 141.5

ጥሩ ስሜት የሚፈጥር የጉልበት ሥራ ለሰብዓዊ ዘር ጤናማ ብርታት የሚሰጥ መድሃኒት ነው፡፡ ደካሞችን ብርቱ፣ ድሆችን ሃብታምና ጎስቋሎችን ደስተኛ ያደርጋቸዋል፡፡ ሰዎች ከሥራ ነፃ በሚሆኑበት ጊዜ ሰይጣን በሆነ በሚስብ ነገር ተሸፍኖ በመቅረብ እድል የሚሰጠው ከሆነ ሊያጠፋቸው አድፍጦ ይጠብቃቸዋል፡፡ ወደ ሰዎች ሥራ በፈቱ ጊዜ መጥቶ የሚከናወንለትን ያህል በሌላ ጊዜ በፍጹም ተሳክተለት አያውቅም፡፡ MYPAmh 142.1