Go to full page →

እርካታ ካለው ሥራ የሚገኝ ትምህርት MYPAmh 142

ሀብት ከሚያመጣቸው ታላላቅ ከፋቶች አንዱ ሥራ ክብርን የሚቀንስ ነው የሚለው ተለዋዋጭ ሐሳብ ነው፡፡ ነቢዩ ሕዝቅኤል ፣‹እነሆ የእህትሽ የሰዶም ኃጢአት ትዕቢት፣ እንጀራን መጥገብ፣ መዝለልና ሥራ መፍታት ነበር፡፡ ይህ በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ላይ ነበር፤ የችግረኛውንና የድሃውንም እጅ አላፀናችም፡፡» ይላል፡፡ ሕዝ 16፡49፡፡ እዚህ ላይ አእምሮን የሚያደክሙ፣ ነፍስን የሚያዋርዱ፣ ማስተዋልን የሚያዛቡና እንደ በረከት ከተሰጠው ነገር እርግማንን የሚፈጥሩ የሥራ-ፈትነት አሰቃቂ ውጤቶች ቀርበውልናል፡፡ ሥራን የሚሰራ ወንድ ወይም ሴት በህይወት ውስጥ መልካምን ታላቅ ነገር ያያል፡፡ ሥራ የሚሰራ ሰው ሃላፊነቶቹን በእምነትና በተስፋ ይሸከማቸዋል፡፡ MYPAmh 142.2

አስፈላጊ በሆኑ የሕይወት ተግባራት ውስጥ እርካታ ካለው ሥራ የሚገኝ ጠቃሚ ትምህርት በብዙ የክርስቶስ ተከታዮች እንደገና ልንማረው የሚገባ ነገር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር በመካኒክነት፣ በነጋዴነት፣ በጥብቅና ወይንም እንደ ገበሬ መሥራት እንደ ታዋቂ ሚሲዮናዊ ሆኖ በፊልድ ውስጥ ከመስራት ይልቅ የክርስትና አስተምሮን ወደ ተራ የህይወት ሥራ መውሰድ የበለጠ ፀጋና ባሕርይን ጠንክሮ መግራትን ይጠይቃል፡፡ የየዕለቱን የህይወት ተግባራትን በመቀደስና እያንዳንዱን ሥራችንን በእግዚአብሔር ቃል መስፈርት መሠረት በመቆጣጠር እምነትን ወደ ሥራ ቦታችንና ወደ ንግድ ሱቃችን ማምጣት ጠንካራ የሆነ መንፈሳዊ አቋምን ይጠይቃል፡፡ ጌታ የሚፈልገው ይህንኑ ነው፡፡ MYPAmh 142.3

ሐዋርያው ጳውሎስ ሥራ-ፈትነትን እንደ ኃጢአት ይቆጥረዋል፡፡ የድንኳን ሥራን በከፍተኛና በዝቅተኛ ዘርፍ ተምሮ ነበር፡፡በአገልግሎቱ ወቅት ብዙ ጊዜ ይህንን ሥራ እየሰራ ራሱንና ሌሎችንም ይረዳ ነበር፡፡ ለዚህ ሥራ ያዋለውን ጊዜ ጳውሎስ እንደባከነ ሰዓት አልቆጠረውም፡፡ ሐዋሪያው የድንኳን ሥራን በሚሰራበት ወቅት በሌላ መንገድ ሊደርሳቸው የማይችላቸውን ሰዎች ያገኛቸው ነበር፡፡ አብረውት ላሉ ሰዎች የእጅ ሥራ ሙያ የእግዚአብሔር ሥጦታ መሆኑን አሳያቸው፡፡ በየዕለቱ ሥራችን እግዚአብሔር መከበር እንዳለበትም አስተማረ ፡፡ በስራ የጠነከሩ እጆቹ እንደ ክርስቲያን አገልጋይ ያሰማ የነበራቸውን በርህራሄ የተሞሉ ተማጽኖዎችን ኃይል አልቀነሱም ነበር፡፡ MYPAmh 142.4

የእግዚአብሔር እቅድ ሁሉም ሰዎች ሠራተኞች እንዲሆኑ ነው፡፡ ከሰነፍ ሰው ልቅ የሚለፋ የጋማ ከብት የመፈጠሩን ዓለማ በተሻለ ሁኔታ ይገልፃል፡፡ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ይሰራል፡፡ መላእክት ሠራተኞች ናቸው፤ ለሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት ናቸው፡፡ የሰማይ ምጣኔ ሐብት ለስንፍና ቦታ ስለሌለው ሥራ የሌለውን ሰማይ የሚጠብቁ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ ነገር ግን ለደካሞችና ሸክማቸው ለከበደባቸው የእረፍት ተስፋ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከድካሙ ወደ ጌታው ደስታ እንዲገባ የሚነገርለት ታማኝ ባሪያ ነው፡፡ የጦር መሣሪያውን በደስታ ያስቀምጥና በክርስቶስ መስቀል ድል ለነሱ በተዘጋጀላቸው ባለ ግርማ እረፍት ውስጥ የጦርነት ጩኸት ይረሳል፡፡ Counsels to Teachrs Parents and Students, P. 274-280. MYPAmh 142.5