Go to full page →

በውሆች አጠገብ ሁሉ መዝራት MYPAmh 143

ጌታ ሕዝቦቹ በተለያየ ሚስዮናዊ የሥራ ዘርፍ እንዲሰማሩና በውሆች አጠገብ ሁሉ እንዲዘሩ እየጠራ ነው፡፡ እርሱ እንድንሰራለት ከሚፈልገው ሥራ በጎሮቤቶቻችንና በጓደኞቻችን መካከል የምንሰራው ትንሹን ክፍል ነው፡፡ ለድሆች፣ ለታመሙትና ላዘኑት ርህራሄን በማሳየት መለኮታዊ እውነት በልባቸው ቦታ እስኪያገኝ ድረስ ተጽእኖ ልናሳድር እንችላለን፡፡ የዚህ አይነት የአግልግሎት ዕድል ሳንጠቀምበት ማለፍ የለበትም፡፡ ይህ ልንሰራ የምንችለው ከፍተኛው ሚስዮናዊ ሥራ ነው፡፡ እውነትን በፍቅርና በርህራሄ ከቤት ወደ ቤት እየዞረ ማድረስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ በመጀመሪያ ሚስዮናዊ ጉብኝታቸው ከሰጣቸው መመሪያ ጋር የሚስማማ ነው፡፡ MYPAmh 143.1