Go to full page →

የሕክምና ሚስዮናዊ ሥራ MYPAmh 143

የህክምና ሚስዮናዊ ሥራ ለአገልግሎት ብዙ እድሎችን ይሰጣል፡፡ በአመጋገብ መሻትን አለመግዛትና ለተፈጥሮ ህጎች ማይም መሆን ዛሬ ያሉትን ብዙ በሽታዎች በማስከተሉ የእግዚአብሔር ህዝቦች እርሱ በፊታቸው ያስቀመጠላቸውን ከፍ ያለ ደረጃ መድረስ አልቻሉም፡፡ ሰዎችን እንዴት በሽታን ማዳን እንደሚቻል ከማስተማር ይልቅ እንዴት ከበሽታ መጠበቅ እንደሚቻል አስተምሩ፡፡ ሰዎች ለራስ ፍላጎት እንዳይገዙ የምናስጠነቅቅ ጠቢብ መምህራን መሆን አለብን፡፡ ባለማወቅ ምክንያት በዓለም ውስጥ የመጣውን ጉስቁልና፣ ቅርጸ-ቢስነትና በሽታ ስንመለከት በድንቁርና ውስጥ ያሉትን ለማስተማርና ከስቃይ ለመገላገል የራሳችንን ድርሻ ከመውጣት እንዴት ቸል እንላለን? MYPAmh 143.4

ወደ ነፍስ የሚወስዱ መንገዶች ስለ ሌሎች ባላቸው ጭካኔ በተሞላበት የተሳሳተ ግምት ስለተዘጉ ብዙዎች ስለ ጤናማ አኗኗር መርሆዎች መሃይም ናቸው፡፡ ለጤና ተስማሚ የሆነ የምግብ ዝግጅትን በማስተማር ጥሩ አገልግሎት መስጠት ይቻላል፡፡ ይህ የሥራ ዘርፍ እንደ ማኝኛውም የሥራ ዘርፍ አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙ የምግብ ዝግጅትን የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች መከፈት አለባቸው፡፡ የተሟላ የምግብ ዝግጅት ሙያን በማስተማር አንዳንዶች ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ መሥራት አለባቸው፡፡ በጤና ተሃድሶ አማካይነት ብዙዎች ከአካል፣ ከአእምሮና ከግብረገብ መዳከም ሊድኑ ይችላሉ፡፡ Review and Harald, June 6, 1912. MYPAmh 143.5