Go to full page →

የመዘመር ስጦታ MYPAmh 143

የመዘመር ሥጦታ ያላቸው ሰዎች ይፈለጋሉ፡፡ ዝማሬ መንፈሳዊ እውነትን በልብ ውስጥ ለማስረጽ ከሚረዱ ውጤታማ መንገዶች አንዱ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በተቀደሰ ዝማሬ ቃላት አማካኝነት የንሰሐና የእምነት ምንጮች ተከፍተዋል፡፡ ወጣትም ሆኑ አዛውንት የቤተክርስቲያን አባላት ይህንን የመጨረሻውን መልዕክት ለዓለም ለማወጅ እንዲሄዱ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ከሄዱ የእግዚአብሔር መላእክት እንዴት በፀሎት ድምፃቸውን ወደ ላይ ማንሳት እንዳለባቸው፣ እንዴት በዝማሬ ድምፃቸውን ማንሳት እንዳለባቸውና የወቅቱን እውነት እንዴት ማወጅ እንዳለባቸው እያስተማሩአቸው አብረዋቸው ይሄዳሉ፡፡ MYPAmh 143.2

ወጣት ወንዶችና ሴቶች እግዚአብሔር ለሚጠራችሁ ሥራ የአዎንታ ምላሽ ስጡ፡፡ ችሎታዎቻችሁን ለመልካም ተግባር እንድትጠቀሙ ክርስቶስ ያስተምራችኋል፡፡ የመንፈስ ቅዱስን የማነሳሳት ኃይል ስትቀበሉና ሌሎችን ለማስተማር ስትሹ አእምሮአችሁ ይታደስና አዲስ የሆኑና ለልባችሁ በተለየ ሁኔታ ያማሩ ቃላትን ለሌሎች ሰዎች ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ MYPAmh 143.3