Go to full page →

ማስተማር MYPAmh 145

ወጣቶችን ለማስተማርና አእምሮአቸውን ለመቅረጽ እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ቤቶች መሰራት ያለባቸውን ባለ ብዙ ዘርፍ ሥራዎች በተሳከ ሁኔታ ለመሥራት ሰዎች ሊያገኙአቸው ከሚችሉአቸው መክሊቶች እጅግ የተሻሉቱ ይፈለጋሉ፡፡ MYPAmh 145.4

መምህራን ያስፈልጋሉ፡፡ በተለይ ለልጆች ረጋ ያሉና ርህሩህ የሆኑ፣ የእነርሱ እርዳታ እጅግ ለሚያስፈልጋቸው ልጆች ትዕግሥትንና ፍቅርን የሚያሳዩ መምህራን ያስፈልጋሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ቤቶች ከፍ ያለ የግብረገብ ብቃት ያላቸውና ሊታመኑ የሚችሉ መምህራን ያስፈልጉአቸዋል፡፡ በእምነታቸው ደህና የሆኑና ችሎታና ትዕግሥት ያላቸው፣ ከእግዚአብሔር ጋር አብረው የሚጓዙና ክፉ ነገር ካለበት ቦታ ሁሉ ራሳቸውን የሚያርቁ መምህራን ይፈለጋሉ፡፡ Testimonies for the Church, vol.6, p. 200-201. MYPAmh 145.5